Flip Your Trip – Downtown – FAQ (AM)

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

ጉዞዎን ይገልብጡ ምንድ ነው?

ጉዞዎን ይገልብጡ ሰዎች ቀንሰው እንዲነዱ ለማበረታታት እና ወዲህ ወዲያ የመዘዋወሪያ ሌሎች መንገዶችን እንዲሞክሩ የሚደግፍ ፕሮግራም ነው።

በ2023 [Flip Your Trip] የት ነው እየተከናወነ ያለው?

በ 2023፣ [Flip Your Trip] በሲያትል መሃል ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ሰፈሮች ውስጥ እየተካሄደ ነው:

 • Uptown
 • South Lake Union
 • Capitol Hill
 • Pike/Pine
 • Denny Triangle
 • Belltown
 • Commercial Core
 • First Hill
 • Pioneer Square
 • Chinatown/International District
 • Pioneer Square

ብቁ የሚሆነው ማን ነው?

ይህ ፕሮግራም የሚከተሉትን ሰዎች ለማገልገል የታሰበ ነው:

 • ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ወደ መሃል ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ሰፈሮች (ካርታ ይመልከቱ) የሚጓዙ።
 • በአሁኑ ጊዜ ወደ መሃል ከተማ ሲመጡ አብዛኛውን ጊዜ ብቻቸውን የሚያሽከርክሩ።
 • ከአሰሪ ነጻ ወይም በቅናሽ የአውቶቡስ ማለፊያ መዳረሻ የለዎትም

ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?

$25 ዶላር የሕዝብ መጓጓዣ መሳፈሪያ ሂሳብ ነው! ይህ በማንኛውም የአካባቢ የሕዝብ መጓጓዣ (አውቶቡስ፣ ቀላል ባቡር፣ ወዘተ) ላይ ሊተገበር ይችላል።
የTransit GO Ticket app መተግበሪያን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ በከተማ ዙሪያ ሁሉ የምታዩትን የጋራ ቀላል ሞተር ብስክሌት እና ኢ-ብስክሌቶችን መጠቀም ይችላሉ።

እንዴት ነው እምመዘገበው?

ወደ FlipYourTrip.org/Downtown ብቁ መሆንዎን ለማረጋገጥ ቀላል ቅጽ በመሙላት ሊመዘገቡ እና በሳምንት ቢያንስ አንድ በመኪና ብቸኛ ጉዞ ለማድረግ በሌላ አማራጭ ለመተካት ቃል መግባት ወደሚችሉበት ይሂዱ። በተመዘገቡ በአንድ ቀን ውስጥ፣ የነጻ ጉዞዎችዎን ለመገምገም ስለሚቀጥሉት እርምጃዎች መረጃ የያዘ የእንኳን ደህና መጣችሁ ኢሜይል ይደርስዎታል።

የORCA ካርዱን ወይስ የTransit GO ቲኬት መተግበሪያን መጠየቅ አለብኝ?

በሚመዘገቡበት ወቅት፣ ቀደም ሲል የተከፈለበት የORCA ካርድ ወይም Transit GO ቲኬት መተግበሪያን ለመጠቀም የ$25 ዶላር የነፃ መሳፈሪያዎችን እንድትመርጡ ይጠየቃሉ። በሚመዘገቡበት ወቅት ምርጫዎን ለመምራት አንዳንድ ከግምት እንዲገቡ የተሰጡ ሀሳቦች እዚህ አሉ።

በሚከተሉት ሁኔታዎች የORCA ካርድ ምርጫ ለእርስዎ ከሁሉም ይልቅ የተሻለ ሊሆን ይችላል:
 • የስማርትፎን ወይም የውሂብ እቅድ ከለሌዎት
 • የተወሰነ የእንግሊዝኛ ብቃት (መተግበሪያው በአሁኑ ጊዜ በእንግሊዝኛ ብቻ ነው የሚገኘው) ካልዎት
 • በቀላሉ የORCA ካርድ የሚመርጡ ከሆነ
 • በጋራ የቀላል ሞተር ብስክሌቶች ወይም ኢ-ቢስክሌቶች ላይ ነፃ የመሳፈሪያ ሂሳቦችን የማግኘት ፍላጎት የላቸውም።
 • በተደጋጋሚ የሕዝብ መጓጓዣ ማስተላለፎችን የሚጠቀሙ (በአሁኑ ጊዜ በ Transit GO መተግበሪያ ውስጥ አይቻልም)
በሚከተሉት ሁኔታዎች የTransit GO ቲኬት መተግበሪያ ለእርስዎ ከሁሉም ይልቅ የተሻለ ምርጫ ሊሆን ይችላል:
 • የስማርትፎን እና የውሂብ እቅድ ካልዎት
 • ለአዳዲስ መተግበሪያዎች ተመችተዋል ወይም አስቀድመው የ Transit GO መተግበሪያ አላቸው
 • የተጋሩ የቀላል ሞተር ብስክሌቶች ወይም ኢ-ብስክሌቶች ላይ ነፃ መሳፈሪያዎች መድረስ ከፈለጉ
 • በእንግሊዝኛ ብቃት ያልዎት ከሆነ

በመስመር ላይ ተመዝግቤያለሁ ግን የእንኳን ደህና መጣችሁ ኢሜይል አልደረሰኝም

በመጀመሪያ፣ “እንኳን ወደ ጉዞዎን ይገልብጡ ደህና መጡ” የሚል ርዕስ ያለው ኢሜይል አሁንም ማግኘት ካልቻሉ፣ ከ  info@FlipYourTrip.org  የአይፈለጌ መልእክት ወይም የቆሻሻ መልእክት ማህደሮችን ይፈትሹ። ለእርዳታ በ info@FlipYourTrip.org ኢሜይል ያድርጉልን።

ለጉዞዎን ይገልብጡ የጉዞ ዘመቻ ዕድሜአቸው ከ19 በታች የሆኑ ልጆች ብቁ ያልሆኑት ለምንድነው?

 • ጉዞዎን ይገልብጡ እድሜያቸው 19 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ አዋቂዎች የታሰበ ነው።
 • ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በታች የሆኑ ወጣቶች አስቀድሞ ለነጻ የሕዝብ መጓጓዣ ብቁ ናቸው፣ እና የመጓጓዣ ድጎማ አያስፈልጋቸውም።
 • የጉዞዎን ይገልብጡ የነጻ መሳፈርን፣ የቀላል ሞተር ብስክሌቶች እና ኢ-ብስክሌት ከተጋሩ ጋር እድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ በሆኑ አዋቂዎች ብቻ ለቀረቡ አቅራቢዎች ሊለወጡ ይችላሉ። ይህ ወጣቶችን እና ሌሎችን ከአካላዊ፣ ከህጋዊ እና ከገንዘብ አደጋዎች ለመጠበቅ/ ከመከላከል በቦታው የተደረገ ነው።

ስለ መጓጓዣ አማራጮቼ አጠቃላይ መረጃ ለማግኘት የት መሄድ እችላለሁ?

የጉዞችዎን አማራጮች ለማሰስ፣ በጉዞዎን ይገልብጡ መነሻ ገጽ ላይ ያሉትን ምርጥ የመረጃ/ የሃሳብ ሀብት ምንጮችን ይመልከቱ

የሳል (Sal) የጉዞ ሜትር/ መለኪያ

2207 የተሰጡ ቃል ኪዳኖች

13238 በዚህ ሳምንት "የተገለበጡ" ጉዞዎች

አውቶቡስ
1790
ቀላል ባቡር / ባቡር / የመንገድ መኪና
1552
የውሃ ታክሲ / የጀልባ መጓጓዣ
290
የራሴን ብስክሌት/ ኢ-ብስክሌት መጋለብ
393
የተጋራ ኢ-የቀላል ሞተር ብስክሌት/ኢ-ብስክሌት
441
በእግር መሄድ
859
መኪና/ መለስተኛ አውቶቡስ መጋራት
347
ሌላ
14