ስለ ጉዞዎን ይገልብጡ
ጉዞዎን ይገልብጡ በሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT) የተጀመረው የሕዝብ መጓጓዣ፣ መሳፈር መጋራት፣ በእግር መሄድ፣ ብስክሌት መጋለብ፣ እና በቀላል ሞተር ብስክሌት መጠቀምን ለማበረታታት እና ለመደገፍ ነው። SDOT የሚያልመው ከከተማዋ ፍትሃዊ እኩልነት፣ ደህንነት፣ ተንቀሳቃሽነት፣ እና ከዘላቂነት ግቦች ጋር ለማጣጣም በነጠላ ተሳፋሪ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን ጥገኝነት ለመቀነስ ነው። የSDOT የመጓጓዣ አማራጮች ቡድን መረጃን ለመስጠት እና በብቸኝነት ለሚያሽከረክሩ ሰዎች አማራጮችን ለማበረታታት የጉዞዎን ይገልብጡ ፕሮግራምን ያስተዳድራል።

ሳል ከተባለው የሳልሞን ዓሣ ጋር ይገናኙ
ሳል ሳልሞን የጉዞዎን ይገልብጡ ፊት እና ድምጽ ነው። ሰዎችን ከብዙ የመገኛ መንገዶች ጋር ለማገናኘት በጣም ትጓጓለች። ከፍላጎቶችዎ ጋር ከሚስማሙ የመጓጓዣ አማራጮች ውስጥ እንድትመራትዎ ይፍቀዱላት!
እስካሁንም ድረስ፣ አጽንዖታችን የነበረው በሰፈር ላይ በአተኮሩ ዘመቻዎች ላይ ሲሆን፣ ይህም መጨናነቅን ለመቀነስ እና ቀልጣፋ ጉዞን ለማበረታታት የሁኔታ-ፈረቃ መፍትሄዎችን በማቅረብ ነበር። ከዚህ በታች ያለፉትን ዘመቻዎቻችንን ይመልከቱ።