የህዝብ ማመላለሻ/መጓጓዣ
ሌላ ሰው መንዳት እንዲያደርግልዎ ይፍቀዱ!በሲያትል ውስጥ በአውቶቡስ፣ የመንገድ መኪናን፣ ቀላል ባቡርን፣ የመመላለሻ ባቡርን፣ የውሃ ታክሲ፣ እና የተሳፋሪዎች ጀልባን ጨምሮ ብዙ የሕዝብ መጓጓዣ አማራጮች አሉ። ስለ የክፍያ አማራጮች፣ መስመርዎን ስለ ማቀድ፣ ስለሚረዱ የሕዝብ መጓጓዣ ፕሮግራሞች እና ስለ ሌሎችም ከዚህ ከታች ይወቁ።
- የተሳፋሪ መሳሪያዎች – የሜትሮ አገልግሎቶችን በመጠቀም ጉዞዎን ለማቀድ እንዲረዳዎ መመሪያ ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ።
- ጉግል ካርታዎች – የመመላለሻ አማራጮችን፣ መስመሮችን፣ የሕዝብ መጓጓዣ መርሃ ግብሮችን፣ እና ከመስመር ውጭ ካርታዎችን ለማየት፣ በተጨማሪ አንድ ቦታን ለመጎብኘት ከሁሉ ይልቅ በጣም ጥሩውን ጊዜ እና ሌሎችንም ፈልገው እንዲያገኙ የጉግል ካርታዎችን ይጠቀሙ። በድህር አሳሽዎ ውስጥ እና በመተግበሪያ ቅርጸት ዓይነት ለAndroid እና ለiPhone ይገኛል።
- *One Bus Away – ለAndroid እና ለiPhone ትክክለኛ የሕዝብ መጓጓዣ ጊዜ መረጃ የሚያቀርብ መተግበሪያ።
- *ሜትሮ የጉዞ ዕቅድ አውጪ – ጉዞ ያቅዱ፣ የሚመጡትን የመነሻ ሰዓቶች ይመልከቱ፣ እና የተሽከርካሪዎችን አቀማመጥ ትክክለኛ ጊዜ ይመልከቱ።
- የ Hopelink Transportation Resource Line – የደንበኞችን ፍላጎቶች፣ የህዝብ ማመላለሻ መስመሮችን፣ እና ግላዊ የሆኑ የጉዞ ዕቅዶችን የሚመጥን ልዩ የሆነ የመጓጓዣ አማራጮችን ለማግኘት የአንድ ለአንድ ድጋፍ ያቀርባል።
- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 9፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ድረስ ክፍት ነው
- ስልክ: 425-943-6760፣ ቅጥያ 2
- ኢሜይል: mobility@hopelink.org
- ጉዞ ለማቀድ እርዳታ ከአንድ ሰው ጋር ለመነጋገር:
- ከሰኞ እስከ አርብ ከንጋቱ 6፡00 እስከ ምሽቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ በኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የደንበኞች አገልግሎት 206-553-3000 ይደውሉ። አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ቋንቋዎን ከሚናገር ሰው ጋር ለመገናኘት 1 ን ይጫኑ። የመስማት ድካም ያለባቸው ተሳፋሪዎች በ 711 WA Relay መደወል ይችላሉ።
- ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 8፡00 እስከ ምሽቱ 6፡00 ሰዓት በ888-889-6368 ለሳውንድ ትራንዚት (Sound Transit) የደንበኛ አገልግሎት ይደውሉ። አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ፣ 1 (800) 823-9230 ይደውሉ እና ቋንቋዎን ይግለጹ። የመስማት ድካም ያለባቸው ተሳፋሪዎች TTY Relay በ 711 መደወል ይችላሉ።
*በእንግሊዘኛ ብቻ
- *ORCA ካርድ – ፑጄት ሳውንድ (Puget Sound) ክልል ውስጥ ላሉ የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት አቅራቢዎች ሁሉ የሚጠቅም ካርድ።
- *ታሪፍ የተቀነሰ ORCA – ስለተቀነሰ የ ORCA ታሪፍ ካርድ ፕሮግራሞች ይወቁ።
- *የወጣቶች ORCA ካርድ – ለሁሉም ተሳታፊ ኤጀንሲዎች በነጻ ለመጓዝ ለወጣቶች 18 ወይም ከዚያ በታች ካርድ
- Transit GO Ticket መተግበሪያ – ለAndroid እና ለአይፎን የክሬዲት ካርድዎን፣ የዴቢት ካርድዎን ወይም ጥሬ ገንዘብዎን በመጠቀም በቀጥታ ለኪንግ ካውንቲ ሜትሮ፣ ለውሃ ታክሲ፣ ለሳውንድ ትራንዚት፣ ለሳውንደር ባቡሮች፣ ለኪትሳፕ ካውንቲ፣ እና ለሲያትል ስትሪትካር ትኬቶች ለመግዛት መተግበሪያ።
- እንዴት እንደሚከፈል: የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ – አውቶብስ፣ ሜትሮ ፍሌክስ እና የውሃ ታክሲ ለመጠቀም ለኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የክፍያ አማራጮች መመሪያ።
- እንዴት እንደሚከፈል: የድምፅ ትራንዚት – ለሳውንደር (Sounder) ባቡሮች፣ ST Express አውቶቡሶች እና ሊንክ (Link) ቀላል ባቡር ለመጠቀም ለሳውንድ ትራንዚት ክፍያ አማራጮች መመሪያ።
*በእንግሊዘኛ ብቻ
ማስታወሻ፡ ለተጓዦች፣ ብዙ ቀጣሪዎች የህዝብ መጓጓዣ ጥቅማ ጥቅሞችን ይሰጣሉ። ለORCA ካርድ ብቁ መሆንዎን ቀጣሪዎን ይጠይቁ።
ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች
- የኪንግ ካውንቲ አገልግሎቶች እና ፕሮግራሞች – በኪንግ ካውንቲ የሚቀርቡ ተደራሽ የተንቀሳቃሽነት አገልግሎቶች ዝርዝር።
- *Hopelink Find a Ride – ለቀድሞ ወታደሮች፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ግለሰቦች እና ሌሎች የመጓጓዣ ግብዓት ምንጮች።
- የ Hopelink Medicaid መጓጓዣ – ለሜዲኬድ (Medicaid) ተቀባዮች ወደ ህክምና ቀጠሮዎች እና ከዚያ መልስም ተሳፍሮ ጉዞዎች።
- Hyde አመላላሾች (Shuttles) – በመላ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኛ አቅመ–አዳሞች የማመላለሻ መጓጓዣ።
- ሜትሮ ፍሌክስ – በዛ ባሉ የኪንግ ካውንቲ ሰፈሮች ውስጥ በጥያቄ የተሽከርካሪ መሳፈሮችን የሚያቀርቡ የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት። በተሽከርካሪ ወንበሮች እና ሌሎች ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች ለደንበኞች ADA ተደራሽ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ይገኛሉ።
*በእንግሊዘኛ ብቻ
- *ትራንዚት 101 – በሲያትል ውስጥ የሕዝብ መጓጓዣን ለመጠቀም ምስላዊ መመሪያ።
- *የመጓጓዣ ካልኩሌተር – የመጓጓዣ ወጪዎችዎን እና ሌላ ዘዴ ለመምረጥ ምን እንደሚያስወጣ ያሰሉ።
- የተሳፋሪ ደህንነት – የሜትሮ አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ወቅት ስለ ደህንነት ማወቅ።
- *ተጨማሪ መረጃ
*በእንግሊዘኛ ብቻ
ይህን
ያውቁ ኖሯል?
70% የሲያትል ቤተሰቦች/ አባወራዎች በ10 ደቂቃ የእግር መንገድ ውስጥ (SDOT) በጣም ወዲያው የሕዝብ መጓጓዣ አውታረ መረብ (በየ 10 ደቂቃ ወይም ከዚያ በተሻለ የሚመጣ) የማግኘት እድል አላቸው።